Welcome

» Core Business

    » Training and Research

    » Archives and Manuscripts Administration

    » National Library Information Resources management

    » Ethiopian Studies and Legal Deposit service

    » Records Management

» Wat's on...

    » Exhibition

    » Public Lecture

» Training

    » E-training

    » Training on demand

» Useful Information

    » Contacts

    » Videos

    » Nala Location

» Registration

    » ISBN Request

    » Record Center

Links

Photo Gallery

» Download Membership Registration Form

1 2 3 4 5 6
11 22 33 44 55 66

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዋና ሰራዎች

መረጃ ለሀገር ልማት፣ለትምህርት ዕውቀት መስፋፋት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መዳበር በተለይም አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለዘመን አቻ የማይገኝለት መሣሪያ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ መረጃ ባግባቡ ተሰብስቦና ተደራጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ከተደረገ የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የተሟላ መረጃ ለማግኘት ደግሞ አብያተመዛግብት፣ አብያተመጻሕፍትና የዶክመንቴሽን ማዕከላት ግንባር ቀደሙን ሥፍራ ይዘው ይገኛሉ፡፡
 ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የሀገሪቱ ብሔራዊ የመረጃ ማዕከል እንደመሆኑ የሀገሪቱን የሥነ-ፅሁፍ ሀብቶችና ቅርሶች በአንድ ማዕከል ስር በማሰባሰብ፣ በማደራጀትና ጥቅም ላይ በማዋልና ጠብቆ ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡

የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመረጃ ሃብቶችን በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግና በአገሪቱ ውስጥ ለሚታተሙ የመረጃ ሃብቶች መዝገበ መጽሐፍ (Bibliography) በማዘገዘጀት የተጠቃሚዎችን የመረጃ ፍላጎት በማርካት የኤጀንሲውን ራእይና ተልኮ ከማሳካት አንጻር የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል፡፡

የስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት

የስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በኤጀንሲው የየዘርፉን ስራዎች በዋናነት የሚከናውኑ ስራዎችን ማለትም በስልጠና ዘርፍ፣ በጥናትና ምርምርና ፖሊሲ ዝግጅት እንዲሁም በህትመትና መድረክ ዝግጅት የሚያከናውኑ ነው፡፡

የሕዝብ ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

በዚህ ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ክፍሎች ያሉ ሲሆን እነዚህም የሰርኩሌሽን፣ የዶክመንቴሽን HIV/ADIS፣ የሥርዓተ ጾታ፣ የኢንተርኔት፣ የኢሜል፣ የሕግ ክምችት ፣የጋዜጣና የመጽሔት፣ የብሬልና የሕጻናት ክፍል ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ጥናትና ህግ ክምችት ዳይሬክቶሬት

ዋና ዋና አገልግሎቶች፡   

-- በአዋጅ 179/91 መሠረት በሀገር ዉስጥ የሚታተሙ የሥነጽሁፍ  ና የስነ -ድምጽ   መረጃ ሀብትን  በአዋጁ መሠረት 3/ሶስት ቅጅ  በመረከብ  ተጠብቀዉ ለትዉልድ እንዲተላለፉ ማድረግ

-- በውጭ ሀገርና በኢትዮጰያውያን ፀሐፊዎች የተጻፉ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ መካከለኛና ዘመናዊ ታሪክ እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የተጻፉና የተተረጐሙ የሥነ ጽሁፍ መረጃዎች፤ በብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋ ዎች  ባህልናታሪክ፣  ላይ ያተኮሩ ፣ ሥራዎች ለጥናትና ምርምር አገልግሎት ማመቻቸት፡፡

-- በግዢ በሚሰባሰቡና በሚደራጁ  የልብወለድና ማንኛዉንም የእዉቀት ዘርፍ መጽሐፍት በኢትዮጵያ ቋንቋ የአማርኛ ክፍል የንባብ  አገልግሎት ላይ እንዲዉሉ  ያደርጋል

-- በሀገሪቱ ለሚታተሙ የመረጃ ሃብቶች የአለም አቀፍ ስታንዳርድ የመጽሀፍት መለያ ቁጥር እንዲያገኙና ለደራሲያንም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት

-- በቡክ ፌር የጋራ ቅንጅታዊ መድረክ ማዘጋጀት  የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎን ማሳደግ

የመዛግብት እና የጽሑፍ ቅርስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የዚህ ዳይሬክቶሬት ዋነኛ አገልግሎት በመዛግብቱ ዘርፍ በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙት መንግስታዊ ከሆኑት መስሪያ ቤቶች በሚሰበሰቡና በሚደራጁ መዛግብት አገልግሎት መስጠት እንዲሁም በቤተመጻሕፍት ዘርፍ ጥንታዊ ጽሑፎችን በማደራጀት አገልግሎት መስጠት ነዉ፡፡

የሪከርድ ስራ አመራር ስርጸት ዳይሬክቶሬት (ብሔራዊ የሪከርድ ሥራ አመራር አገልግሎት  ዳይሬክቶሬት)

ዳይሬክቶሬቱ በጥናት ላይ በመመስረት በመንግስት ተቋማትና በልማት ድርጅቶች ዘመናዊ የሪከርድ ሥራ አመራር ሥርዓት በመዘርጋት ሪከርዶች ከአፈጣጠራቸው እስከሚወገዱበት ወይም በመዛግብትነት ተመርጠው ወደ ቤተመዛግብት እስከሚዛወሩበት ባለው የሪከርድ የህይወት ዑደት በአግባቡ ወጪ ቆጣቢ በሆነ አሰራር ተደራጅተውና ተይዘው በሚጠበቀው ደረጃ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ለማስቻል ተሞክሮዎችንና ደረጃዎችን በመቀመር፣ የህግ ማዕቀፎች ልዩ ልዩ መመሪያዎችና የአሰራር ማንዋሎችን በማዘጋጀት ፣ ግንዛቤ በማስጨበጥ ፣ በመተግበር ፣ በመከታተልና በመገምገም ዘመናዊ አሰራር እንዲሰፍን ይሰራል፡፡ በዘርፉ የሚታየውን ሰፊ የአመለካከትና የግንዛቤ ችግሮችን ለመፍታት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ይሰራል ፣ አዳዲስ ተሞክሮዎችን ያስፋፋል፡፡

የኢትዮጵያ ጥናትና ህግ ክምችት አገልግሎት

መረጃ ለሀገር ልማት፣ለትምህርት ዕውቀት መስፋፋት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መዳበር በተለይም አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለዘመን አቻ የማይገኝለት መሣሪያ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ መረጃ ባግባቡ ተሰብስቦና ተደራጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ከተደረገ የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Read More» 

የብሄራዊ ቤተመጻሕፍት የመረጃ ሃብቶች አስተዳደር

መረጃ ለሀገር ልማት፣ለትምህርት ዕውቀት መስፋፋት፣ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መዳበር በተለይም አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለዘመን አቻ የማይገኝለት መሣሪያ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ መረጃ ባግባቡ ተሰብስቦና ተደራጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ከተደረገ የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

Read More» 

የሪከርድ ስራ አመራር ስርጸት

የስልጠና እና ጥናትና ምርምር 1

Read More» 

የህዝብ ቤተመጻሕፍት አገልግሎት

News

Downloads