በዚህ ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ክፍሎች ያሉ ሲሆን እነዚህም የሰርኩሌሽንና ኤሌክትሮኒክስ ክፍል፣ የዶክመንቴሽን ክፍል  HIV/AIDS ዴስክ  የሥርዓተ ጾታ፣ የኢንተርኔት  የኢሜይል፣ የኤሌክትሮኒክስ ላይብረሪና የወቅታዊ ጋዜጦችና መጽሔቶች፣ የብሬልና የሕጻናት ቤተመጻሕፍት ክፍል ናቸው፡፡

 1. የሰርኩሌሽን ክፍል  

በዚህ ክፍል የሚገኙ ስብስቦች - የተለያዩ የማጣቀሻመጻሕፍት፣ የንባብ መጻሕፍት፣ የቪዲዮ ካሴት፣ዲቪዲ፣ እና ልዩ ልዩ የፈተና ወረቀቶች ናቸው፡፡
 በዚህ ክፍል  የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-

 • የውሰት አገልግሎት
 • የአጭርና የረዥም ጊዜ  የንባ አገልግሎት  የምክርና የፎቶ ኮፒ አገልግሎት

የአባልነት ምዝገባ፡-

 • የተገልጋዮችን ልዩ ፍላጎት መሠረት ያደረገ የመረጃ አገልግሎት፣ አዳዲስ የገቡ መጻሕፍትን  የማስተዋወቅ  እናቤተመጻሕፍቱን አስመልክቶ ለተገልጋዮች ገለጻ የማድረግ አገልግሎት፣

ተጠቃሚዎች፡፡-

 • ተመራማሪዎች
 •  መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች  ሠራተኞች
 •  ተማሪዎች                                                  

የአገልግሎት ሰዓት፡

             ከሰኞ - እሁድ  24 ሰዓት አገልግሎት

             በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 የመረጃ ምንጮች፡-

 • የተለያዩ የማጣቀሻ መጻሕፍት
 •  የንባብ መጻሕፍት  የቪዲዮ ካሴት
 •  ዲቪዲ፣ እና ልዩ ልዩ የፈተና ወረቀቶች

 አገልግሎት - የውሰት፣ የአጭርና የረዥም ጊዜ ንባብ፣ የምክር፣ የፎቶ ኮፒ፣ የአባልነት ምዝገባ፣የተገልጋዮችን ልዩ ፍላጎት መሠረት ያደረገ የመረጃ አገልግሎት፣ አዲስ የገቡ መጽሐፍት የማስተዋወቅ ሥራ እናቤተመጻሕፍቱን አስመልክቶ ለተገልጋዮቹ ገለጻ የማድረግ አገልግሎት፣

 ተጠቃሚዎች - ተመራማሪዎች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች

የሥራ ሰዓት፡                          

         ከሰኞ - እሁድ 24 ሰዓት አገልግሎት

         በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 1. የዶክመንቴሽን ክፍል -

በዚህ ክፍል  የሚገኙ  የመረጃ ምንጮች፡-

 • የተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች (FAO, worldBank, UNESCO) ወዘተ  ጽሑፎችና ሪፖርቶች

የሚሰጡ አገልግሎቶች፡

 • የንባብና የፎቶ ኮፒ አገልግሎት
 • የምክር አገልግሎት
 •  የተገልጋዩን ልዩ ፍላጎት መሠረት ያደረገ የመረጃ አገልግሎት፣

ተጠቃሚዎች 

 • ተመራማሪዎች
 •  መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች  ሠራተኞች

 ተማሪዎች
የአገልግሎት ሰዓት፡

        ከሰኞ - እሁድ 24 ሰዓት አገልግሎት

        በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 1. የመጽሔትና የጋዜጣ ክፍል

  በዚህ ክፍል የሚገኙ  የመረጃ ምንጮች  

 • የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ወቅታዊ መጻሕፍትናጋዜጦች

የሚሰጡ አገልግሎቶች፡

 • የንባብ እና የፎቶኮፒ አገልግሎት

ተጠቃሚዎች  

 • መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኖች 
 •  ተማሪዎች

የአገልግሎት ሰዓት፡

           ከሰኞ-ዓርብ፡ ከጠዋቱ 245-ምሽቱ 130
          
ቅዳሜና እሁድ ከጠዋቱ 300 - ምሽቱ 1200

 1. የኢንተርኔትና የኢ-ሜይል ክፍል -በዚህ ክፍል  የሚሰጡ አገልግሎቶች
 • የኢንተርኔትና የህትመት አገልግሎት
  ተጠቃሚዎች -
 • ተመራማሪዎች
 •  ተማሪዎች
 •  መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
 •  ሠራተኞች 

የአገልግሎት ሰዓት፡
                    

ከሰኞ - እሁድ 24 ሰዓት አገልግሎት

በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 1. የኤች አይ /ኤድስ ዴስክ እና የሥርዓተ ጾታ ክፍል በዚህ ክፍል የሚገኙ

 የመረጃ ምንጮች፡-

 • በኤች አይ /ኤድስ እና በስርዓተ ጾታ የተጻፉ ልዩ ልዩ ጽሁፎች፣ ሪፖርቶች፣ የድምጽና የምስል መረጃዎች፣ 

 በክፍሉየሚሰጡ አገልግሎቶች፡ 

 • የንባብ አገልግሎት፣ የፎቶ ኮፒ አገልግሎት፣የድምፅናየንባብአገልግሎት

ተጠቀሚዎች፡ 

 • ተመራማሪዎች
 • ተማሪዎች
 • መንግሥታዊናመንግሥታዊያልሆኑድርጅቶችሠራተኞች፣

የአገልግሎት ሰዓት፡-

ከሰኞ - እሁድ 24 ሰዓት አገልግሎት

በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 1. የብሬል ክፍል -

የሚሰጡ አገልግሎቶች - የንባብ አገልግሎት
ተጠቀሚዎች፡-

 • ተመራማሪዎች
 • ተማሪዎች
 • መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
 • ሠራተኞች፣

የአገልግሎት ሰዓት፡                    

ከሰኞ - እሁድ 24 ሰዓት አገልግሎት

በህዝብ በዓላት ቤተመጻሕፍቱ አገልግሎት አይሰጥም

 1. የሕፃናት ክፍል

 የመረጃ ምንጮች - የተለያዩ የማጣቀሻ መጻሕፍት

 • ELT የውሰት አገልግሎት

የሚሰጡ አገልግሎቶች - የንባብ እና DVD አገልግሎት
ተጠቀሚዎች -

 • ህፃናት
 • ወላጆች

 በዳይሬክቶሬቱ  የሚሰጡ  አገልግሎቶችን  ለማግኘት   ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች -

 • ማንኛውም የቤተመጻሕፍቱ ተጠቃሚ የተሰጠውን የአባልነት መታወቂያ በዋናው በር ላይ ላሉ የጥበቃሠራተኞች አሳይቶ መግባት አለበት
 • የቤተመጻሕፍቱ አባል የሆነ ማንኛውም ግለሰብ ሌሉች ሰዎችን ወይም ቤተሰቦቹን ወክሎ መጽሐፍ(መጻሕፍት)መዋስ አይችልም፣
 • አባላት የተሰጣቸውን የአባልነት መታወቂያ ለሌላ 3 አካል አሳልፈው መስጠት አይችሉም
 •  የግል መገልገያ ንብረቶች ወደ ቤተመጻሕፍት ቤቱ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
 •  የግል ንብረቶችን በዋናው በር መግቢያ ላይ ለዚህ ዓላማ  የተዘጋጀ ቦታ ላይ  ለጥበቃ ሠራተኞች ሰጥቶ መግባትይቻላል
 • የቤተመጻሕፍቱ ተገልጋዮች በጥበቃ ሠራተኞች ዘንድ ንብረታቸውን በሚያስቀምጡበት ወቅት ለዚህ አገልግሎትየተዘጋጀውን ኮድ መውሰድ አለባቸው፡፡
 • ይህ ሣይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ክፍተት ኤጀንሲው ተጠያቂ አይሆንም፡፡

 የውሰት  መመለስ ስርዓት -

 • አባላት የሚዋሷቸውን ማቴሪያሎች የተሟሉና በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ መሆናቸውን አረጋግጠው መዋስአለባቸው፣
 •  ይህ ሳይሆን ቀርቶ ማቴሪያሎች በሚመለሱበት ጊዜ ለተጓደሉትና በጥሩ ሁኔታ ላይ ላልተመለሱት ማቴሪያሎች  የተዋሰው አካል   ተጠያቂ ይሆናል
 • በቅጣት ላይ ያለ አባል የቅጣት ክፍያውን ሣይከፍል  ምንም ዓይነት  መጽሐፍ መዋሰ አይችልም፣
 •  ቤተመጻሕፍቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውአባላት የተዋሱትን  ማቴሪያል የመመለሻው ቀን ከመድረሱ በፊትየማስመለስ መብት አለው፣
 1. የሪዘርቬሽን እና እድሳት ክፍል፡-
 • መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያለሆኑ ድርጅቶች አባላት ብር 75( ሰባ አምስት ብርለሪዘርቤሽን አገልግሎትይከፍላሉ.
 •  DVD አና የፈተና ማቴሪያሎችን ለተጨማሪ ጊዘ ማደስ አይቻልም፣

  ቅጣት

 • አባላት የተዋሱትን ማቴሪያል በተባለው ቀን የመመለስ  ግዴታ አለባቸው  በተባለው ቀን የማይመልሱ ከሆነ ግን ለሁሉም መጻፍሕት እና ለኦዲዮ ማቴሪያሎች ብር .75 ይከፍላሉ(ብር ዜሮ ሰባ አምስት )ይከፍላሉ
 • ለሁሉም የቪዲዮ እና DVD  የውሰት አገልግሎት ብር 1.75 ይከፍላሉ፡፡

 የጠፉና የተበላሹ ንብረቶችን በተመለከተ፡-

 • አባላት የተዋሷቸውን ማቴሪያሎችና የአባልነት መታወቂያ ካርዳቸውን በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው፡፡
 • ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጠፉት እና  ለተጎዱት ማቴሪያሎች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ይከፍላሉ፡፡

ለጠፉ ወይም ሙሉ በሙሉ ለተበላሹ፡-

 • የተዋሷቸውን ንብረቶች ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ ካቆዩ የንብረቱን 5ይከፍላሉ፣
 •  ለአንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ሳይመለሱ ለቆዩ ንብረቶች የንብረቶችን 1ዐዐይከፍላሉ፣
 •  የተጎዱ ነገር ግን መጠገን ለሚችሉ ንብረቶች ብር 25.ዐዐ /ሃያ አምስት ብርይከፍላሉ
 •  ለጠፉ ወይም ለተበላሹ የአባልነት መታወቂያ ካርዶች ብር 15.ዐዐ /አሥራ አምስት ብርይከፍላሉ
 • አባላት የተዋሱት ማቴሪያል ወይም የአባልነት መታወቂያ ካርዳ ከጠፉ ወዲያውኑ ለቤተመጻሕፍቱ ሪፖርትማድረግ አለባቸው፡፡
 • ይህ ሳይሆን ቀርቶ በካርድ ሌላ ሰው ቢዋስበት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

 ንብረት አጠቃቀምን በተመለከተ -

 • ከቤተመጻሕፍቱ የተዋሱትን Home video, DVD ለሌላ 3 ወገን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም ኮፒ ማድረግበጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
 •  በቤተመጻሕፍቱ ውስጥ በተዘጋጀው /Video cassette recorder/ የተዋሱትን Video ጥራት አረጋግጦ መዋስ አለበት፡፡
 • የቤተሰብ ኃላፊዎች የሚዋሱትን ማቴሪያል ለህፃናት እንደ እደሜ ደረጃቸው የሚመጥን መሆኑን በኃላፊነት  ስሜት መዋስ  አለባቸው፡፡

 የአባልነት እድሳትን በተመለከተ

 • የአባልነት ጊዜያቸውን የሚያድሱ የቤተመጻሕፍቱ አባላት የተዋሱትን ማቴሪያል እና  የአባልነት ክፍያቸውንእንዲመልሱና ህጋዊ የሆነ መልቀቂያ እንዲወስዱ ይጠየቃሉ፡፡

 ከአባልነት መሰናበት፡

 • አባላነት ከቤተመጻሕፍት አባልነታቸው  በሚከተሉት ምክንያቶች ከአባልነት ይሰናበታሉ፡፡
 • በተደጋጋሚ ጊዜ የተዋሷቸውን መጻሕፍት በወቅቱ  ሳይመልሱ ሲቀሩ፣
 • ማንኛውንም የማታለልና የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ
 • በቤተመጻሕፍቱ ሠራተኞች ላይ የማመናጨቅ ሁኔታ ካሳዩ
 • የቤተመጻሕፍት አባልነታቸውን  የሰረዙ፣
 • ለጠፉና ለተጎዱ ንብረቶች ክፍያ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸው ያልከፈሉ
 • የአገልግሎት ጊዜያቸውን ላሳለፉና ቅጣት ሳይከፍሉ ከቀሩ
 • የቤተመጻሕፍቱን ንብረቶች ያላአግባብ መጠቀም፣
 • የተዋሷቸውን ንብረቶች ከመመለስ ይልቅ በሌላ ተመሳሳይ ማቴሪያል ለመመለስ መሞከር፣
 • የቤተመጻሕፍቱን አገልግሎት  ካወኩ፣
 • የአባልነት መታወቂያቸውን  ለሌላ አሳልፎ ከሰጡ