Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page
Back

ህዝበ ገለጻ (public lecture) ተካሄደ(ነሐሴ 7/2012 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ሐሙስ ነሐሴ 7/2012 .  « ባሕላዊ  የእንሰሳት ሕክምና  ከየት ወዴት » በሚል ርዕስ በዓለም ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የኮሮና / COVID-19 / ቫይረስን ለመከላከል በአካል ጥቂት ሰዎችን ተሳታፊ በማድረግ እና የዙም አፕሊኬሽንን በመጠቀም ሕዝበ ገለጻ አካሒዷል፡፡

በሕዝበ ገለጻው መድረክም « ባሕላዊ  የእንሰሳት ሕክምና  ከየት ወዴት » በሚል ርዕስ ጽሑፉ ያቀረቡት ዶክተር  ታፈሰ መስፍን በጽሑፋቸው ፡- አለምአቀፍ  ባህላዊ  የእንሰሳት  ህክምና ታሪክ መቼ እንደተጀመረባህላዊ እንሰሳት ህክምና የሚገኝበት ሁኔታ፣ባህላዊ  የእንሰሳት ህክምና  እንደ ሰው ባህላዊ  ህክምና   በሚገባ እንደማይታወቅ፣ባሕላዊ የእንሰሳት ሕክምና አዋቂዎችዘመናዊ የእንሰሳት ህክምና አጀማመር፣ዘመናዊ የእንሰሳት ህክምና የተጀመረው የደስታ በሽታን ለመቆጣጠር በተደረገው ሂደት እንደሆነ ማጣቀሻ ሲሰጡ፡-

 • 1903 የመጀመሪያ ላቦራቶር በአስመራ እንደተከፈተ
 • 1908-1914 የፈረንሳይ መንግስት የደስታ ክትባት ጉለሌ ላይ ከነበረው ላቦራቶር እንዳካሄደ
 • ደስታን ለመቆጣጠር 1924 አለም አቀፍ ድርጅት OIE በፈረንሳይ መቋቀዋሙንና
 • ኢትዮጵያ በሽታውን ለመቆጣጠር ሁለት ትላልቅ ዘመቻዎች እንዳካሄደች JP15 1970-1976  እና PARC 1989-1997 .ኤ. 2008 ኢትዮጵያ ከደስታ በሽታ ነጻ እንደወጣች ገልፀው አክለውም ገና  በቁጥጥር ያልዋሉ ብዙ በሽታዎች እንዳሉም በፅሑፋቸው ጠቁመዋል፡፡

በጽሑፋቸውም ዘመናዊ የእንሰሳት ህክምናን በኢትዮጵያ ለማሳደግ በመንግስት የተደረጉ ጥረቶች ሲጠቁሙ

 • 1900:  የግብርና / መመስረቱን፣
 • 1920 : ሁለት ኢትዮጵያውያን የእንሰሳት ሀኪሞች ወደ ሀገር መመለሳቸውን
 • 1940:  የደስታ በሽታን ለመቆጣጠር 312 የእንሰሳት ጤና ተቀጣጣሪዎች እንደሰለጠኑ
 • 1963: የጉለሌ የእንሰሳት ህክምና ላቦራቶር ወደ ደብረዘይት እንደተዛወረ
 • 1965: የመጀመሪያ ረዳት የእንሰሳት ሀኪሞች መመረቃቸውን
 • 1979: የመጀመሪያው  የእንሰሳት ህክምና ኮሌጅ መመስረቱን
 • በአሁኑ ወቅት ወደ 14/አስራ አራት/ ኮሌጆች እንደደረሱም በጽሑፋቸው ጠቁመዋል፡፡

ባህላዊ የእንሰሳት ህክምና የሚጠቀምባቸው ግባቶችን በተመለከተ ሲናገሩ ከእንሰሳት የሚገኙ አካሎች  ለምሳሌ፡- የጃርት ስጋ ወተት እንዲሁም ከእንሰሳት የሚገኙ ስብ (ሞራ) ፤ እጽዋት እና ማዕድናት የቦሌ/ ቦጂ አፈር እንደሆኑም አስገንዝበዋል፡፡

ባህላዊ ሕክምና ለዘመናዊ ህክምና ያበረከተው እውቀትንም በስፋት ሲያነሱ፣ ባህላዊ የእንሰሳት ህክምና ጠንካራ ጎኖች፤የባህላዊ እንሰሳት ህክምና ተግዳረቶች፤የግጦ መሬት እያነሰ በመሄዱ እንሰሳት ከተለያዩ  ሰፈር በመሰባሰብ ለተላላፊ በሸታ  እየተጋለጡ እንደሆነና መፍቴ ሊበጀትለት እንደሚገባ ጠቁመው ቆሻሻ የሚበሉ እንሰሳትን
ለእንሰሳት  የምናደርገው  እንክብካቤ ትኩረት ስለሚጎለው ትኩረት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የባህላዊ የእንሰሳት ህክምናን ለማሳደግ የተደረጉ ጥረቶች (የቻይና ባለሞያዎች)

 • የቻይና(Taiwan-formosa) የእንሰሳት ህክምና ልኡካን በኢትዮጵያ ቆይታቸው 1974-1978 ( ) 23,000 እንሰሳትን በክትባትና በህክምና በባህር ዳር፤ በኮምቦልቻና በመቀሌ ላቦራቶሮችና ክሊኒኮች፤ አገልግሎት ማድረጋቸው፡፡
 • እንዲሁም 22 መድሃኒቶችን በሃገራችን ከሚገኑት እፅዋቶች ቀምመው  ጥቅም ላይ ማዋላቸው፤
 • ለምሳሌ መተሬ በበግ የኮሶ ትል ላይ ውጤት ማሳየቱን
 • አኩፐንክቸር በተወሰኑ (የእንሰሳት በሽታዎ ችላይ ተጠቅመው ጥሩ ውጤት እንደተገኘበት ሪፖርት እንዳደረጉ (hernia, sarcoma, conjuctivitis)
 • በኢትዮጵያ ባህላዊ የእንሰሳት ህክምና እድገት ውድቀት ያሳየበት ጊዜ እንደሆነም በጽሑፋቸው ጠቁመዋል፡፡

ባህላዊ የህክምና አሰጣጥ ዘዴዎችንም ሲገልጹ ፡-አፍ መጋት፣በአፍንጫ መጋት ቆዳን በመብጣት መድሃኒት መቅበር ቆዳን በመተኮስ እንዲሁም በመቀባት፣በመውለጃ በር መድሃኒት ማስገባት፣በእበት መውጫ እና በአይን እንደሆነም በጽሑፋቸው አስፍረዋል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያም የሀገራችን ገበሬዎች የዘመናዊ ህክምናን አገልግሎት በበቂ ደረጃ እንደማያገኙም በጥናታቸው አስፍረው በመቶኛም ሲያስቀምጡ፡-80%  የሚሆነው ገበሬ የዘመናዊ ህክምና ተጠቃሚ እንዳይደለ እና የኬንያን ልምድ ብንወስድ፡- 40 ሚሆኑ የእንሰሳት ሃኪሞች፣ የባህላዊ እውቀት ያላቸው እንሰሳት አርቢዎች፤ የጹሑፍ ችሎታ ያላቸው ሰዎች፤ ስእል መስራት የሚችሉ ሰዎች፤ ሌሎችም በጉዳዩ ያገባናል የሚሉ ተሰባስበው ያዘጋጁት መጽሀፍ እንዳለ ተናግረው፤ ይህንን ሂደት በሃገራችንም እውቅና ሰጥተን የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ በማደራጀተ እንቅስቃሴ መደረግ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

ባህላዊ እንሰሳት ህክምና የሚገኝበት ሁኔታ ሲገልጹም በሐገራችን 80 በመቶ የሚሆነው ገበሬና እንሰሳት አርቢ የሚጠቀመው በዚሁ ባህላዊ ህክምና ሲሆን የሀገሮች ኢኮኖሚ  እየተሻሻለ ሲሄድ ይሄ ዕውቀት እየተዳከመ በመሄድ ላይ እንዲገኝ አንስተዋል፡፡

ከእንሰሳት ወደ ሰው ከሰው ወደ እንሰሳት የሚተላለፉ  በሽታዎች ምሳሌነት ሲያስቀምጡም፡-የእብድ ውሻ በሽታ፣የአባ ሰንጋ በሽታ፣የሳንባ በሽታ (TB)የኮሶ ትል፣እንደሆኑም ጠቁመው

አሁ ሰዓት ኢትዮ ፤ኡጋነዳ፤ ህንድ እና ኔዘርላነድ በጋራ የተገበሩ እንዳሉና ፕሮግራም  ቅስቃሴዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል ሕንድ፤ ኢትዮጵያ (ESAP) ኔዘርላንድ፤ እና ኡጋንዳ    በጋራ በባህላዊ የጡት በሽታ ህክምና፤ በእርባታ፤ በወተት ጥራት ላይ በጋራ እየሰሩ እንዳሉም ተናግረው  (Antibiotic Reduction in Milk) ዋነኛው ዓላማ በዘመናዊ የጡት ህክምና በወተቱ ውስጥ የሚከሰተውን የአንቲባዮቲክን መጠን መቀነስ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የባህላዊ መድሐኒት አዘጋገጀትንም በስፋት አቅርበው ጽሑፍ አቅራቢው በማጠቃለያቸው በመጀመሪያ የአመለካከት ለውጥ መኖር እንዳለበትና ሌላው አለም ጥሎን ሲሄድ ዝም ብለን ማየት እንደሌለብንና በዘመናዊ ዕውቀት ብቻ ሁናታዎችን  ማሻሻል እንደማይቻልና እውቀቱ ከአዋቂዎች በወቅቱ ወይም በአንዳንድ ማህበረሰብ ሚስጢር ሆኖ ስለሚያዝ እና ስለማይመዘገብ ከተፈጥሮ ሀብት መመናመን ይልቅ የባህል አዋቂዎች መመናመን ሀገርን ስለሚጎዳ በፍጥነት እውቀትን መመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመው አዋቀዎቹ ሲሞቱ ቀጣይነቱ እንደሚጠፋ ተናግረው በመግቢያቸው እንደጠቆሙት ሀገራችን  የብዙ ብሔረሰቦችና የተለያየ ስነምህዳር የተለያዩ ዕጽዋት ያላት ሀገር በመሆና ብዙ ዕውቀቶች የጠፉ እንደሆነ በመገመት በመጥፋት ያሉትን ማዳን ይኖርብናል ብለው  አክለውም ይህን የማህበረሰብ ዕውቀት የሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት አውቅና ሊሰጡት እንደሚገባና  በየኮሌጆች ስልጠና ሊኖር እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ዶክተሩ በጽሑፋቸው መጨረሻም የኮና ቫይረስ ታሪክን ሲናገሩ የመጀመሪያው ኮሮና ቫይረስ በዶሮ ላይ 1930 እደተገኘና፤ ቀጥሎም የመጀመሪያው በሰው ላይ የተገኘው ኮሮና ቫይረስ 1960 መሆኑን፣ኮሮና ቫይረሶች ጉንፋንን በተለይም በቅዝቃዜ ወቅት እንደሚያመጡሁሉም ኮሮና ቫይረሶች ቀላል በሽታ ብቻ እንደማያመጡምSARS (Severe Acute Respiratory Syndrome) በመጀመሪያ የተገኘው 2002-2003. SARS በአሁኑ ጊዜ ካለው ወረርሽኝ COVID-19 ተመሳሳይነት እንዳለው10 ዓመት ኃላ 2012 (MERS (Middle East Respiratory Syndrome) በሳውዲ አረቢያ እንደተከሰተ በጽሑፋቸው መጨረሻ በማቅረብ ወቅቱን በተመለከተና ኮሮና ቫይረስ ድሮም እንደነበረ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡

በዕለቱ የዶ/ር ታፈሰ መስፍን አወያይ በመሆን የተሳተፉት በሙያቸው ለሀገራቸው በርካታ ስራዎችን ያበረከቱና የናቹራል ላይፍ እስቶል ፋርሚንግ አስተባባሪ የነበሩና በዛው ዘርፍ ኢንተር ናሽናል ሲነር ሪሰርቸር፣ከ30 ዓመት በላይ በእንሰሳት እርባታና ግጦሽ ልማት ተመራማሪና መምህር ፣በኢትዮጵያ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ አባልና የግብርና ቡድን አባል እና ማሪል የሚባል የግል ድርጅት ባለቤትና ም/ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው ገብሩም የጽሑፉን ሐሳብ በማዳበር ከተሳታፊዎች ጥያቄ፣ሐሳብ አስተያት እንዲነሳ አድርገው በአካል ስፍራው በመገኘት ከተሳተፉትና ከዙም አፕሊኬሽንን ተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በመመለስና አስተያየቶችን በመቀበል ሕዝበ ገለጻው ተጠናቋል፡፡