Asset Publisher Asset Publisher

Return to Full Page
Back

የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን ለማስፋፋትና ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲስ መልክ ስራ ሊጀምር ነው፡፡(ነሃሴ 15/2012 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት ሲሰራ የነበረውን የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን ለማስፋፋትና ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በአዲስ መልክ አጠናክሮ መስራት ሊጀምር እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ኤጀንሲው ከሚያክናውናቸው በርካታ ተግባራት አንዱ ከክልሎች እና ከከተማ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ዮኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የንባብ ሳምንት በማዘጋጀት ታላላቅ  እና ታዋቂ ሰዎችን በመጋበዝ ለትውልዱ የንባብ ባህላቸውን በማካፈል  አንባቢ ትውልድ በመፍጠር ለሀገሩ የሚጠቅም ዜጋ እንዲሆን የማድረግና ይህንኑ ልምድም ወደ ማረሚያ ቤቶች በመውሰድ በማረሚያ ቤቶችም ታራሚዎች በቆይታቸው እራሳቸውን ሊለውጡ የሚችሉ መጻሕፍትን እንዲያነቡ መፅሐፍ በመለገስ እንዲያነቡ የማድረግ ስራ ሲሰራና ታራሚዎች ፍርዳቸውን ጨርሰው ወደ ማሕበረሰቡ ሲቀላቀሉ አስተማሪ እንጂ ወደቀደመው ተግባራቸው እንዳይገቡ ለለውጥ እየተጋ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

ታዲያ ይህንኑ ተግባርም ወደማሕበረሰቡ በመውሰድ ለማስረጽ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ቢዘልቅም በዓለም ላይ በተፈጠረው በኮሮና ኮቪድ 19/ቫይረስ ሳቢያ ይህንኑ ሰፊ ተግባሩን እንዳቋረጠ ይታወቃል፡፡ ሆኖም  ዛሬም ይህንኑ ተግባር ለማጠናከር፣ለማሳደግና ለማስፋፋት በአዲስ መልክ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር በጎተራ ፣በየካ ቁጥር 1፣በጎፋ መብራት ኃይል እና በጀሞ ቁጥር 1 የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎትን ለማስፋፋትና ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በዚህ ወቅት በኮሮና /ኮቪድ 19/ቫይረስ ምክንያት በቤት ተቀምጦ ስለሚገኝ በንባብ አእምሮውን እንዲያሳድግና በዕውቀት እንዲያበለጽግ በአዲስ መልክ በተጠናከረ ሁኔታ ለማከናወን ከነሐሴ 15/2012 ዓ.ም አገልግሎት ለመጀመር በማቀድ ከላይ የተዘረዘሩትን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ስራውን በጋራ ለማስጀመር ይረዳ ዘንድ በጎተራ ኮንዶሚኒየም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት በማዘጋጀት ስራው በይፋ እንዲጀመር ተደርጓል፡፡

በዝግጅቱም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖዓምላክ መዝገቡ፣የኤጀንሲው የስራ ክፍል ዳይሬክተሮችና የሚመለከታቸው ፈጻሚዎች የወረዳ 4 ስራ አስፈጻሚዎች አቶ ታዮ ሽፈራው ዋና ስራ አስፈጻሚ፣አቶ አወቀ ጉአ የት/ት ጽ/ቤት ኃላፊ እና አቶ ብርሃኑ አሰፋ የወጣችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የጎተራ፣የካ ቁጥር 1፣የጎፋ መብራት ኃይል እና የጀሞ ቁጥር 1 ኮንዶሚኒየም ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

 

በዕለቱ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጎተራ ኮንዶሚኒየም  ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በቀለ እውነቱ እንደተና ገሩት ይህ ዓይነት ስራ ሲሰሩ ብዙ ችግሮች ሊያጋጥሙ ቢችሉም ለዛሬ እዚህ መድረስ የሁሉም በጎ የሆነ ርብርብ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡በመቀጠልም የጎተራ ኮንዶሚኒየምን አመሰራረትን በተመለከተ በአቶ ተግባር ዘሪሁን በስፋት ተገልጿል፡፡

በዕለቱ የተገኙት ስራ አስፈጻሚ አቶ ታዮ ሽፈራው ጎተራ ኮንዶሚኒየም ነዋሪው ከኮሚቴው ጋር ያለውን ቁርኝት ለለውጡ እንደጠቀማቸው እና አመራሩም የሚፈልገውን ልማት ለመስራት እንደሚቀለው ተናግረው በዘንድሮው የክረምት ወቅትም ከሁለት ሺህ በላይ የጌጥና የምግብ ችግኝ እንደተተከለ እና በጸጥታም ዙሪያ ከዚህ በፊት አካባቢው ችግር እንዳለበት ገልጸው ወንጀለኞችንም እየያዙ እንደሚገኙ ተናግረው ቤተ-መጻሕፍቱ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ሲተጉ የነበሩትን አመስግነው አክለውም በአካባቢው ትምህርት ቤት ለመክፈት ከዚህ በፊት የተጀመረ ነገር እንዳለ እና ለት/ቤት መስሪያነት ህገወጥ መሬት በመንግስት የተያዘ እንዳለና አስፈቅደው ለመስራት የቦታ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖዓምላክ መዝገቡ አባቶቻችን ሲናገሩ በሚል የአባቶች ንግግር ንግግራቸው የጀመሩት ከተማ የሚሰራው ጫካ ተመንጥሮ ነው፡፡ ነገር ግን ጫካ ተመንጥሮ ቤት ካልተሰራበት ቢቀር ይሻል ነበር፡፡ ቤት ብዙ ነገርን ገላጭ እንደሆነ እና አገልግሎት ካልሰጠ የአውሬ መኖሪያ ቢሆን ይሻል ነበር ይላሉ በማለት የቤትን ጥቅም በስፋት ከተለያዩ ነገሮች ጋር በማገናኘት ገልጸው አክለውም የወረዳ አመራሮች ነዋሪዎች በሚሰሯቸው ልማት ላይ አብሮ በመስራትና በቅርበት ያገባኛል ብሎ መገኘት ያልተለመደ እንደሆነ ተናግረው ለተነሳሽነታቸው ምስጋና እንደሚቸረው ብለዋል፡፡  

አክለውም ኃላፊው የጎተራ ኮንዶሚንየምን አባላቶች በዚህ ግዜ ይህ ተግባር በጋራ እንዲካሄድ በቀናነት መፍቀዳቸውንና ሌሎች ተሳታፊዎችንም አመስግነው መስከረም ለህጻናት የት/ት መጀመሪያና የሚፈልጉትን የሚያገኙበት አዲስ ዘመንን የሚያበስር በመሆኑ ሁሌም  እንደሚናፍቁት ገልጸው የኮሮና ቫይረስ በጉዝ ነገሮች ላይም እንደሚቆይ ጠቁመው ይህንኑ ቫይረስም ለመከላከል የጤና ሚኒስተር የሚሰጣቸውንም መልዕክቶች/መመሪያዎች/ ሳይዘነጋ መጽሐፉን ሲዋሱ በልባድ ለብደው ተጠቅመው ሲመልሱ የለበዱበትን በማንሳት እና ሳኒታዝድ በማድረግ መጠቀም እንዲችሉ የማድረግ ስራ በመስራት ጊዜያቸውን በንባብ እንዲሳልፉ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም ከኤጀንሲው በስጦታ የቀረቡ ዋጋቸው አርባ ሺህ የሚገመቱ የተለያዩ ይዘት ያላቸው 200 መጻሕፍቶችን የኤጀንሲው የህዝብ ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ተፈራ ለአቶ ተግባር ዘሪሁን አስረክበው ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡