Back

ለማንበብ ቃልኪዳን የተገባባቸው የፓናል ውይይቶች

የካቲት 2011 ዓ.ም

የጎንደርን የፓናል ውይይቶች ልዩ የሚያደርጋቸው ተሳታፊው በብዛት መገኘቱና ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት መስጠቱ ነው፡፡ በሌሎች ቦታዎች ከሚጠራው ተሳታፊ ሶስት አራተኛው እንደሚመጣ መገመት የተለመደ ነው፡፡ በጎንደር ግን ከተጠበቀው ታዳሚ በሶስት አራተኛ ጨምሮ መገኘቱ አስገርሟል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በውይይቱ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ ለውይይት የቀረበው ጉዳዩ ምንያህል ቁጭት እንዳሳደረባቸው ለመታዘብ ችለናል፡፡

ለውይይት ከቀረቡት መነሻ ጥናቶች መካከል በት/ቤቶች የንባብ ክበባት መቋቋም የሚኖረው ፋይዳ ፣ አብተ መጻህፍት ለንባብ መዳበር እና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ፣ በንባብ እና በክበባት ምስረታ ላይ የታዋቂ ደራሲንና አርቲስቶች ምክር፣ አብያተ መዛግብት ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ለሕዝባዊ ትስስር መዳበር ያላቸው ሚና፣ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የህትመት አዘገጃጀትና አሰባሰብ በሚሉ ርዕሶች ርዕሦች ላይ የቀረቡ የሚሉ ጥናታዊ ጽሑፎች ይገኙበታል፡፡ አቅራቢዎቹም በዘርፉ ጠለቅ ያለ እውቀትና ልምድ ያላቸው ከጎንደር ከዩኒቨርሲቲ፣ ከኮድ ኢትዮጵያ ሃላፊ፣ ከኢፌድሪ ፓርላማ የቤተመጻህፍት ሃላፊ፣ ከኤጀንሲው ከሚገኙ ማህበራት የተጋበዙ ይገኙበታል፡፡

አወያዮቹም አንቱ የተባሉ ደራሲያንና አርቲስቶች በመሆናቸው መድረኩን በጥበብ መርተውቷል፡፡ ውይይቱንም ተሳታፊውን በሚመጥን መልኩ አስኪደውታል፡፡ ከዚህም በላይ ታዳሚው ክበባትን ለመመስረት፣ በክበባት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን እንዲሁም አንብቦ ለመለወጥ ቃል የተገባበት መድረክ በመሆኑ ውጤታማ ስራ ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

የአብያተ መጽሐፍት መጠናከር አንባቢ ማህበረሰብ ለመፍጠር የማይተካ ሚና ያለው ስለሆነ ይህንኑ ለማጠናከር ኤጀንሲያችን 1100 መጽሐፍትን ለጎንደር ከተማ /ቤቶች እንዲሁም የጎንደር ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በአጠቃላይ 4033 የተለያየ ይዘት ያላቸውን መጽሐፍት በጎንደር ከተማና በዙሪያዋ ለሚገኙ /ቤቶች በስጦታ አበርክተዋል።

በመቀጠልም የቤተመጻህፍት ሙያተኞች ማኅበር አስፈላጊነት ላይ ተወያይቶ ለመመስረት እና አጠናክሮም ለመቀጠል የመከረ ሲሆን ለዚሁም መሟላት የሚገባአቸው ቅድመ ሁኔታዎቸ ላይ በስፋት ለመነጋገር ተወስኗል፡፡ ይህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ እየተነሳ ወደተግባር ሳይገባ የቆየ እንደነበር ገልው አሁን ላይ መነሳቱና መቋጫ ማግንት መቻሉ እንዳስደሰታቸው ታዳሚዎቹ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል አምስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡ እነዚህም  የሪከርዶች ፋይዳ ለመልካም አስተዳደር በሚል ርዕስ በአቶ ግርማ አበበ፣ የአብያተ መዛግብት  መቋቋም አስፈላጊነትና የዩንቨርሲቲዎች ሚና በሚል ርዕስ በአቶ ገረመው ከበደ፣ጥንታዊ የመዛግብት ዓይነት፣ ጠቀሜታ እና አሁን ያሉበት ሁኔታ፣ ወ/ሪት አድሴ ያለው ከጎንደር ዩንቨርሲቲ፣የጽሑፍ ሀብቶች አያያዝና አጠባበቅ በሚል ርዕስ በአቶ ስለሺ ሽፈራው ከብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

የኪነ-ጥበብ ምሽት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ

ኪነ-ጥበብ ለጎንደር ህዝብ ባህሉ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከያዝናቸው መርኃ ግብሮች መካከል አንዱና ዋነኛው የኪነ-ጥበብ ምሽት ነበር፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የተካሄደውን ይህንን ዝግጅት በርካታ ተማሪዎች ተካፍለውታል፡፡ ዝግጅቱ አዝናኝና አስተማሪ እንዲሁም ብዙዎችን ወደዚህ ዘርፍ የሳበ ነበር፡፡ የአራተኛ እና የሶስተኛ ዓመት የትያትር ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች በግጥም፣ በመነባንብ እና በተውኔት ስራዎቻቸውን ለውድድር አቅርበዋል፡፡ 

በዕለቱ ታዋቂውና የበርካታ መጽሐፍት ደራሲ የሆነው በአሁኑ ወቅት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቲያትር መምህር ዳንኤል ወርቁ እና ታዋቂ ደራሲና አርቲስት አንዱአለም አባተ ለታዳሚው የሕይወት ተሞክሯቸውንና እውቀታቸውን አካፍለዋል፡፡ ለተወዳዳሪ ተማሪዎችም ሙያቸውን እንዲያሳድጉት ምክር ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ኤጀንሲው ሁሉንም ተወዳዳሪዎች ለማበረታቻ የመጽሐፍት ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

 


News Archive News Archive

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 21 results.